
ባሕር ዳር: ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ በመሬት መደርመስ አደጋ ጉዳት የደረሰባቸው ወገኖችን አደጋው የደረሰበት ስፍራ ላይ በመገኘት አጽናንተዋል፡፡
እንደ ኢቢሲ ዘገባ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በአደጋው ሕይዎታቸውን ባጡ ወገኖች የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን ገልጸው ተጎጂዎችን አጽናንተዋል፡፡
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በትናንትናው ዕለት በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይዎታቸውን ላጡ ዜጎች ከዛሬ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን ማወጁ ይታወቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!