
ጎንደር: ሐምሌ 20/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ መንግሥት ለልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ያሳየውን ቁርጠኝነት የሚደግፍ እና ያሉ ችግሮች ተሻሽለው አስተማማኝ ሰላም እንዲመጣ የሚጠይቅ ሰልፍ እየተካሄደ ነው።
“ለሰላም ዘብ እንቆማለን፤ የተጀመሩ ልማቶችን እናስቀጥላለን” በሚል መሪ ሃሳብ በድጋፍ ሰልፉ ሕዝቡ ዘላቂ ሰላም እና ልማትን ለማምጣት የሚያደርገውን ጥረት እንደሚያስቀጥል ተመላክቷል።
በሰላማዊ ሰልፉ “የጎንደር እና አካባቢው የረጅም ጊዜ የልማት ጥያቄዎች ምላሽ ለመስጠት ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትራችን፣ እሳቸው የሚመሩት ፖርቲ እና መንግሥት ያሳዩንን ቁርጠኝነት እውቅና እንሰጣለን” የሚሉና ሌሎች ሃሳቦች እየተገለጹ ነው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!