
ባሕር ዳር: ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ከኢራን የወጣቶች ሚኒስትር ዴኤታ ሲና ካልሆር ጋር ተወያይተዋል።
በኢትዮጵያና በኢራን ወጣቶች መካከል ድልድይ የሚኾን መደላደል ማመቻቸት በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ መምከራቸውም ተገልጿል።
በውይይታቸውም በአይሲቲ፣ በቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ላይ በትብብር ለመሥራት ተስማምተዋል።
የኢትዮጵያ ወጣቶች ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ፉአድ ገና ከብሪክስ የወጣቶች ጉባኤ ጎን ለጎን ከብሪክስ አባል ሀገራት የወጣት ሚኒስትሮች ጋር የሁለትዮሽ ውይይት እያደረጉ እንደሚገኙ ከኢትዮጵያ ወጣቶች ካውንስል የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!