በፈረንሳይ የባቡር ትራንስፖርት ተቋረጠ።

11

ባሕር ዳር: ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገረ ፈረንሳይ በባቡር ሀዲዶች ላይ በተፈጸመ ጥቃት የባቡር አገልግሎት ተቋርጧል፡፡ ይህን ተከትሎም ዛሬ አመሻሽ ላይ የሚጀመረው የፓሪስ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥነ ሥርዓት እንደሚዘገይ ነው የሮይተርስ እና ዴይሊ ሜይል መረጃዎች ያመለከቱት፡፡

የሀገሪቱ ባቡር ትራንስፖርት ድርጅት ጥቃቱን “ኾን ተብሎ” የተፈጸመ ነው ብሎታል፡፡ ዓላማውም ዛሬ አመሻሽ የሚደረገውን የፓሪስ ኦሎምፒክ መክፈቻ ውድድር ለማስተጓጎል ነው በሚል ኮንኖታል፡፡

በመኾኑም ወደ ኦሎምፒክ የመክፈቻ ሥፍራው ለመጓዝ ቲኬት የገዙ ሰዎች ጉዟቸውን እንዲያራዝሙም ተጠይቀዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleጤናን፣ ሰላምን፣ አንድነትን እና ፍቅርን ታሳቢ ያደረገ ስፖርታዊ ውድድር በሀራ ከተማ ተካሄደ።
Next articleበግል ባለሃብቶች የሚለሙ ሰፋፊ የእርሻ ቦታዎች አሁን ላይ የት ናቸው?