“በበጀት ዓመቱ ከ57 ቢሊዮን ብር በላይ ገቢ ተገኝቷል” የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት

28

አዲስ አበባ: ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ የባሕር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ አገልግሎት ድርጅት የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥቷል።

ጋዜጣዊ መግለጫውን የሰጡት የተቋሙ ዋና ሥራ አሥፈፃሚ በሪሶ አመሎ (ዶ.ር) ድርጅቱ በ2016 በጀት ዓመት ለማግኘት አቅዶ ከነበረው 51 ነጥብ 6 ቢሊዮን ብር 57 ነጥብ 14 ቢሊዮን ብር መሠብሠብ መቻሉን ነው የገለጹት።

የውጭ ምንዛሬ ገቢን ለማሳደግ በተሠራው ሥራም በበጀት ዓመቱ 420 ነጥብ 67 ሚሊዮን ዶላር ተገኝቷል ብለዋል። ተቋሙ ካሉት 10 መርከቦች በተጨማሪ በቀጣይ ስድስት መርከቦችን ለመግዛት ማቀዱንም ዋና ሥራ አሥፈፃሚው በመግለጫው ጠቅሰዋል።

የዩክሬን ሩሲያ ጦርነት እና የእስራኤል ሐማስ ጦርነት በዘርፉ ላለው እንቅስቃሴ ፈተና ኾኖ መቆየቱን ዋና ሥራ አሥፈፃሚው አስገንዝበዋል በሀገሪቷ አንዳንድ አካባቢዎች ያሉት ግጭቶች እና አለመረጋጋቶችም ሌላኛው በዘርፉ ያጋጠሙ ተግዳሮቶች እንደነበሩ አንስተዋል።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ለምግብ የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የሀገራችንን እድገት ማረጋገጥ ይገባናል” በለጠ ሞላ (ዶ.ር)
Next articleጤናን፣ ሰላምን፣ አንድነትን እና ፍቅርን ታሳቢ ያደረገ ስፖርታዊ ውድድር በሀራ ከተማ ተካሄደ።