
ባሕር ዳር: ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “የምትተከል ሀገር፣ የሚያጸና ትውልድ” በሚል መሪ መልዕክት የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር እና የተጠሪ ተቋማት መሪዎች በኮምቦልቻ ከተማ አሥተዳዳር የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር አካሂደዋል።
የኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር በለጠ ሞላ (ዶ.ር) እንደተናገሩት የኮምቦልቻ ከተማ የኢንዱስትሪ መናኽሪያ የኾነች እና እምቅ የተፈጥሮ ሃብት ያላት በመኾኑ ችግኞችን በመትከል ጥቅም ላይ እንዲውሉ ማድረግ ይገባል ብለዋል።
“ለምግብ የሚውሉ የፍራፍሬ ችግኞችን በመትከል የምግብ ዋስትናን በማረጋገጥ የሀገራችንን እድገት ማረጋገጥ ይገባናል” ነው ያሉት፡፡ የአማራ ክልል ምክትል ርዕሰ መሥተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር) በበኩላቸው በክልሉ እስካሁን ከ1 ነጥብ 4 ቢለዮን በላይ ችግኞች መተከላቸውን ተናግረዋል። የተተከሉ ችግኞች እንድጸድቁ የግብርና ባለሙያዎች እና አርሶ አደሮች ክትትል እና ጥበቃ ሊያደርጉ ይገባል ብለዋል፡፡
ከችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ጎን ለጎን የአቅመ ደካሞችን ቤት መልሶ የመገንባት ሥራም አስጀምረዋል፡፡
ዘጋቢ፦ ሰይድ አብዱ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!