
ባሕር ዳር: ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ጎጃም ዞን የተሰማራው የምሥራቅ ዕዝ ክፍለጦር መንግሥት ያቀረበውን የሰላም አማራጭ ባልተከተሉ ታጣቂዎች ላይ እርምጃ በመውሰድ አመራሮቹን ጨምሮ 31 የቡድኑ አባላት ተደምሰዋል ብሏል።
ከሕዝቡ እያገተና እየዘረፈ ባለ ንብረቶቹን ገንዘብ ካላመጣችሁ እያለ ሲደራደርበት የነበረው 02 አይሱዙ ኮልድሮም የጫነ 01 ኤፍ ኤሳር መኪና ቡና የጫነ ከነ ሹፌሩና ረዳት፤ 01 ግሌደር 01 ስካቫተር 04 ደብል ጋቢና ፒካፕ 03 ሲንግል ጋቢና ፒካፕ 06 ሞተር ሳይክል 01 ባጃጅ 09 የጦር መሳሪያና ሌሎች ቁሶች መማረኩን ገልጸዋል፡፡
የክፍለጦሩ አዛዥ ኮሎኔል አለሜ ታደለ ለሠራዊቱ በሰሜን ጎጃም ሰፊውን ቀጣና የይልማና ዴንሳ ወረዳ ደቡብ ቋሪት፤ ደቡብ ደጋ ዳሞት፤ ምሥራቅ ሞጣን በማካለልና ፅንፈኛው በማፅዳት ዋሸራ ከተማ ላይ መሽጎ ሕዝቡን ሲዘርፍ፣ ሲያግትና ሲያሻውም እየገደለ የሚረካ ታጣቂ ቡድን ላይ ጥቃት መፈጸማቸውን ተናግረዋል፡፡
የክፍለጦሩ አዛዥ እንደተናገሩት በጎንጂ ቆለላና የይልማና ዴንሳ ወረዳዎች ስር የሚገኙ ደብረ ዋይፋት እና የገበታ የተባሉ የገጠር ቀበሌዎች የፀጥታ ኀይሉ ረዥም ጊዜ ያልገባባቸው በመኾኑ ታጣቂ ቡድኑ ከተለያዩ ቦታዎች የሚያግታቸውና የሚዘርፋቸውን የሕዝብ ንብረት የሚያከማችበት ዋሸራ ከተማ አካባቢ መስርቶ የነበረው ካምፕ ላይ ድንገተኛ ኦፕሬሽን በማድረግ ከፍተኛ ሰብዓዊና ማቴሪላዊ ኪሳራ አድርሰንበታል ብለዋል፡፡
ሠራዊቱ በፈጸመው ኦፕሬሽን
1ኛ.ሙሉሰው ሰንደቁ ሻለቃ አመራር
2ኛ. ሙሉሰው ወለላው ሻለቃ አመራር
3ኛ. መጣልኝ ጤናው ሻለቃ አመራር ሲሆን
04. ሻምበል አመራር የተመደቡ የታጣቂው መሪዎች ላይ እርምጃ መውሰዳቸውን ኮሎኔል አለሜ ታደለ ተናግረዋል፡፡
የክፍለጦሩ ሬጅመንቶች ባደረጉት ኦፕሬሽን ከታጣቂ ቡድኑ እገታ የተለቀቁት ቡና ጭኖ የታገተ የኤፍ ኤስ አር ሹፌር አቶ ሳሙኤል ጌታቸው ሹፌርና ወንድማገኝ ካሳ ረዳት ታጣቂዎቹ ካገቱን በኋላ ከባለ ንብረቱ ጋር በአንድ ሚሊዮን ብር ሲደራደሩ እንደነበር ተናግረው ለሕይወታቸው የደረሰላቸውን
የመከላከያ ሠራዊት ማመሥገናቸውን ከመከላከያ ሠራዊት ማኅበራዊ ትስስር ገጽ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!