“ኢትዮጵያ የወንዞች ሀገር ናት” ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ

16

ባሕር ዳር: ሐምሌ 19/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባጋሩት መልእክት “ኢትዮጵያ የወንዞች ሀገር ናት” ብለዋል።

ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸውም የተፋሰስ ምክር ቤትን በጸሐፊነት ከሚመሩት የውኃ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አመራሮች ጋር ውይይት አካሂደናል ነው ያሉት፡፡

በውይይታችንም በኢትዮጵያ ተፋሰሶች ገፅታ ተግዳሮቶች እና ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ዙሪያ ምክክር አድርገናል ብለዋል፡፡

በቀጣይ ሀገሪቱን ተጠቃሚ የሚያደርግ የተቀናጀ የውኃ ሃብት አስተዳደርን ለመገንባት በምክር ቤት ደረጃ ትኩረት ተሰጥቶባቸው ሊሰሩ በሚገባቸው ዋና ዋና ተግባራት ዙሪያ ተወያይተን መግባባት ላይ ደርሰናል ነው ያሉት፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሀገሪቱ የጋራ ችግሮች ላይ መፍትሄ ለማበጀት የአካል ጉዳተኞችም መምከር አለብን” ዋና ዳይሬክተር ዓባይነህ ጉጆ
Next articleበሰሜን ጎጃም ጎንጂ ቆለላ ወረዳ ዋሸራ ከተማ በተደረገ ኦፕሬሽን 31 ታጣቂዎች ተደመሰሱ፡፡