የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በቤንሻንጉል ጉሙዝ ክልል የአጀንዳ ማሠባሠብ መርሐ-ግብር እያካሄደ ነው፡፡

14

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በአሶሳ ከተማ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ውስጥ በመካሄድ ላይ በሚገኘው በዚህ መርሐ ግብር የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍል ተወካዮችን በማሳተፍ እየተካሄደ ነው፡፡

ኮሚሽኑ ከዚህ ቀደም አከናውኖ በነበረው በተወካዮች መረጣ ሂደት ላይ የተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎችን እንዲወክሉ ከየወረዳው የተመረጡ ተወካዮች በአደራ ይዘው ባመጡት የአጀንዳ ሃሳብ ላይ በቡድን ተከፍለው ውይይቶችን እያካሄዱም ይገኛሉ፡፡

10 የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመወከል ውይይት እያደረጉ የሚገኙ ተወካዮች 420 ናቸው። ተወካዮቹ ከ3 ዞኖች፣ ከ27 ወረዳዎች እና ከ 1 ልዩ ወረዳ የተውጣጡ ስለመኾናቸው ነው የተገለጸው።

የኅብረተሰብ ተወካዮቹ ተወያይተው የተስማሙባቸውን የአጀንዳ ሃሳቦች በቃለ ጉባኤ በመፈራረም ለቀጣዩ መድረክ ያዘጋጃሉ ተብሏል፡፡

በሂደቱ እነዚህ ተወካዮች የተስማሙባቸውን አጀንዳዎች ወደ ቀጣዩ የአጀንዳ ማሠባሠብ ሂደት በአደራ የሚያቀርቡላቸውን ስድስት ተወካዮች ይመርጣሉ ተብሎም ይጠበቃል፡፡

በመጪዎቹ ቀናት የተመረጡ ተወካዮች ከሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በመኾን የአጀንዳ ሃሳቦቻቸው ላይ ውይይት ማድረግ እንደሚጀምሩ ከሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየግድቡ መሠረት ድንጋይ ከተጣለበት ጀምሮ 20 ቢሊዮን ብር ገደማ ተሰብስቧል።
Next article“የሀገሪቱ የጋራ ችግሮች ላይ መፍትሄ ለማበጀት የአካል ጉዳተኞችም መምከር አለብን” ዋና ዳይሬክተር ዓባይነህ ጉጆ