የአማራ ክልል አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የባሕር ዳር ስታዲየምን እየጎበኙ ነው።

77

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የተመራ የአማራ ክልል ምክር ቤት ቡድን የባሕር ዳር ስታዲዬምን እየጎበኘ ነው።

የባሕር ዳር ዓለም አቀፍ ስታዲየም ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እየተገነባ ነው። በአማራ ክልል ምክር ቤት የስታዲየሙን የሥራ እንቅስቃሴ ነው እየተመለከቱ ያሉት።

የስታዲየሙን የሥራ እንቅስቃሴ የአማራ ክልል ወጣቶች እና ስፖርት ቢሮ ኀላፊ እርዚቅ ኢሳ እያብራሩላቸው ነው።

የባሕር ዳር ስታዲየም ሲጠናቀቅ ስደተኛውን የኢትዮጵያን ብሔራዊ ቡድን ወደ ሀገሩ ይመልሳል። ለባሕር ዳር ከተማ የስፖርት ቱሪዝም እንቅስቃሴ ማደግም ከፍተኛ ድርሻ ይኖረዋል ተብሎ ይጠበቃል።

የምክር ቤት አባላቱ በስታዲየሙ ክልል ውስጥ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ23 ሚሊየን በላይ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ዙሪያ መወያየታቸው ተገለጸ።
Next article“ከስድስት ሚሊዮን ኩንታል በላይ የአፈር ማዳበሪያ ወደ አርሶአደሮች ማሳ ደርሷል” ግብርና ቢሮ