ከ23 ሚሊየን በላይ የተለያዩ የማኅበረሰብ ክፍሎች በክልሉ ወቅታዊ የጸጥታ ችግር ዙሪያ መወያየታቸው ተገለጸ።

27

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ክልሉ የገጠመውን የጸጥታ ችግር በሰላም ለመፍታት ሰፊውን የማኀበረሰብ ክፍል በማወያዬት አዎንታዊ ግብረ መልሶች ተገኝተዋል።

የአማራ ክልል አሥተዳደር ጉዳዮች ክላስተር የተቋማትን የ2016 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም እና የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ ዝግጅት ግምገማ በባሕር ዳር ከተማ እየተካሄደ ነው።

በግምገማ ወቅት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የአሥተዳደር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ኀላፊ ደሳለኝ ጣሰው እንዳሉት ከ23 ሚሊዮን በላይ የማኀበረሰብ ክፍልን ክልሉ ስለገጠመው የጸጥታ ችግር እና የሰላምን አስፈላጊነት በማወያየት ሰፊ ፋይዳ ተገኝቶበታል ብለዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየመኮይ-ማጀቴ መንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾነ።
Next articleየአማራ ክልል አፈ ጉባኤ ፋንቱ ተስፋዬ የባሕር ዳር ስታዲየምን እየጎበኙ ነው።