
ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በክልሉ መንግሥት የበጀት ድጋፍ የተያዙ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክቶች በትኩረት እየተሰሩ ይገኛል።
በክልሉ በመንገድ ቢሮ ባለቤትነት እና በገጠር መንገድ ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የሚገነባው መኮይ-ማጀቴ የመንገድ ግንባታ ፕሮጀክት ተጠናቅቆ ለአገልግሎት ክፍት ኾኗል።
የግንባው ሦስት ከፍተኛ እና መካከለኛ ድልድዬች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት ክፍት ኾነዋዋል። በተጨማሪም የማሳለጫ መንገድን ግንባታው እንደተጠናቀቀ ከገጠር መንገድ ኮንስትራክሽን ኤጀንሲ የተገኘው መረጃ ያመላክታል።
ኤጀንሲው የግንባታ ፕሮጀክቶቹ ተጠናቅቀው ለአካባቢው ማኅበረሰብ አገልግሎት እንዲሰጡ ድጋፍ ላደረጉ የአካባቢው ማኅበረሰብ፣ አመራሮች እና ለኤጀንሲው ሠራተኛች ምስጋና አቅርቧል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!