
ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በማዕከላዊ ጎንደር ዞን በላይ አርማጭሆ ወረዳ የረጅም ጊዜ የኅብረተሰብ ጥያቄ የነበረው የድልድይ ግንባታ ጥያቄ ምላሽ አግኝቷል፡፡
ማህና በተሰኘ ወንዝ ላይ የተገነባው የተንጠልጣይ ድልድይ 120 ሜትር ርዝመት ያለው ነው፡፡ ድልድዩ የኅብረተሰቡ የረዥም ጊዜ ጥያቄ የነበረ ሲኾን ለአገልግሎት በመብቃቱ ኅብረተሰቡ መደሰቱን ገልጿል፡፡ ይህ የእግረኛ ተንጠልጣይ ድልድይ በወረዳው ሰባት ቀበሌዎችን እንደሚያገናኝ ነው የተገለጸው፡፡
ግንባታው በክልሉ መንገድ ቢሮ፣ ሄልቬታስ በተሰኘ መንግሥታዊ ባልኾነ ድርጅት እና በኅብረተሰቡ ተሳትፎ ነው የተገነባው፡፡
ተንጠልጣይ ድልድዩ መገንባቱ ለአካባቢው ማኅበረሰብ የሚኖረው ኢኮኖሚያዊ እና ማኅበራዊ ፋይዳ የጎላ እንደኾነ ከማዕከላዊ ጎንደር ዞን የመንግሥት ኮሙኒኬሽን መምሪያ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!