
ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት ናዳ ሳቢያ ጉዳት ለደረሰባቸ ወገኖች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጉን አስታውቋል።
ድጋፉ የተደረገው የባንኩ የሥራ ኃላፊዎች እና ሠራተኞች በግላቸው እያደረጉ ካለው ድጋፍ በተጨማሪ የተደረገ ድጋፍ መኾኑን ከባንኩ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!