የኮሌራ በሽታ እንዳይከሰት የቅድመ መከላከል ሥራዎችን እያከናወነ መኾኑን የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡

33

ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በክረምት ሊከሰቱ ከሚችሉ በሽታዎች መካከል ኮሌራ አንዱ ነው፡፡ ይህንን በሽታ ለመከላከልም አስፈላጊ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች እየተሰሩ መኾኑን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡ የመምሪያው ምክትል ኅላፊ ተፈሪ ይደነቅ እንዳሉት የኮሌራ በሽታ የግል እና የአካባቢ ንጽህናን በተገቢው መንገድ ባለመጠበቅ የሚከሰት ነው፡፡

በተለይም ምግብን አብስሎ በመመገብ እና ውኃንም በውኃ አጋር አክሞ በመጠቀም የኮሌራ በሽታን መከላከል እንደሚጠበቅ ምክትል ኅላፊው ተናግረዋል። የዞኑ ጤና መምሪያም አስፈላጊ የጥንቃቄ ሥራዎችን እየሠራ ነው ያሉት አቶ ተፈሪ ኅብረተሰቡ መሰል የጤና ችግሮችን እንዳያስተናግድ የግል እና አካባቢ ንፅህናውን መጠበቅ እንዳለበትም መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

ዘጋቢ፦ ፋንታነሽ መሃመድ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article48 ሚሊዮን ብር የሚገመቱ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ማስወገድ መቻሉን የደሴ ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ገለጸ።
Next article“ከዳግም ምርጫ እራሴን ያገለልኩት ለፓርቲው እና ለሀገሬ አንድነት በማሰብ ነው” ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን