
ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የደሴ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የጤና መምሪያ ኀላፊ ሰኢድ የሱፍ እንዳሉት በከተማ አሥተዳደሩ በመንግሥት እና በግል መድኃኒት ቤቶች ከ10 ዓመት በላይ ተቀምጠው የቆዩ እና ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶችን ማስወገድ ተችሏል።
መድኃኒቶቹ 48 ሚሊዮን የሚገመቱ ናቸው። ከዚህ ውስጥ 42 ሚሊዮን ብር የሚገመቱት መድኃኒቶች ከግል ጤና ተቋማት የተሠበሠበ ነው።
መድኃኒቶቹ በአካባቢ እና በማኅበረሰቡ ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ናቸው። ከንግዱ ማኅበረሰብ ጋር በመቀናጀት አካባቢውን በማይበክል እና በማኅበረሰቡ ላይ ጉዳት በማያስከትል መንገድ በተለየ ቦታ ላይ ማስወገድ መቻሉን ነው ያነሱት።
ከተማ አሥተዳደሩ ጊዜያቸው ያለፈባቸው መድኃኒቶች ሥጋት እንዳይኾኑ እየተሠራ መኾኑንም ነው ኀላፊው የገለጹት።
ጊዜያቸው ያለፈባቸውን መድኃኒቶች በጥንቃቄ በወቅቱ እንዲወገዱ ማድረግ እንደሚገባም አሳስበዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!