
ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ እና ቁሳቁስ ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ገዜ ጎፋ ወረዳ መላኩን ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ ኬቾ ቀበሌ ባጋጠመ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የሚሆን የመጀመሪያ ዙር ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ እና ቁሳቁስ የሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ቦታው መላኩን አስታውቀዋል።
ከንቲባዋ ባስተላለፉት መልእክት ወገኖቻችን በደረሰባቸው አደጋ የተሰማኝን ጥልቅ ሀዘን እየገለፅኩ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር እና ሕዝቡ ሁሌም ከጎናችሁ መሆኑን ላረጋግጥላችሁ እወዳለሁ ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!