“ያለፈው በጀት ዓመት ጥንካሬ እንደ መስፈንጠሪያ ድክመቶችን ደግሞ ለማረም ያስችላል” ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር)

31

ባሕር ዳር: ሐምሌ 18/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአማራ ክልል የገጠር ዘርፍ ተቋማት የ2016 በጀት ዓመት ዓመታዊ የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ ተጀምሯል።

በግምገማ መድረኩ የተገኙት በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ዘርፍ አሥተባባሪ እና የግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) ባለፈው በጀት ዓመት የገጠሩ ዘርፍ በችግር ውስጥ ኾኖ ልማትን ማስኬድ መቻሉን ተናግረዋል። “የግምገማ መድረኩ ያለፈው በጀት ዓመት ጥንካሬ እንደ መስፈንጠሪያ ድክመቶችን ደግሞ ለማረም ያስችላል” ብለዋል።

ከግምገማው ማግስትም በ2016 ያመለጡንን ተግባራት አካተን በ2017 የበጀት ዓመት ጠንክረን ሠርተን የሕዝባችን የመልማት ጥያቄ እንመልሳለን ነው ያሉት። ግምገማዊ ውይይቱ ለሁለት ቀናት የሚቆይ ሲኾን በዘርፉ ሥር የሚገኙ የገጠር ዘርፍ ተቋማት ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም ሪፖርት ቀርቦ ውይይት እንደሚደረግበት ይጠበቃል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየአማራ ክልል ንግድ እና ገበያ ልማት ቢሮ የኑሮ ውድነቱ እንዳይባባስ የጀመረውን ሥራ አጠናክሮ እንዲቀጥል ቋሚ ኮሚቴው አሳሰበ።
Next articleየአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከ45 ሚሊዮን ብር በላይ የገንዘብ እና ቁሳቁስ ሰብዓዊ ድጋፍ ወደ ገዜ ጎፋ ወረዳ ላከ።