
ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከስፔን የውጭ ጉዳይ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ሚኒስትር ዴኤታ ዲያጎ ማርቲኔዝ ጋር በጽሕፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
አምባሳደር ታዬ ከሚኒስትር ዴኤታው ዲያጎ ማርቲኔዝ ጋር የኢትዮጵያ እና ስፔን የሁለትዮሽ ግንኙነትን የበለጠ ማጠናከር በሚቻልባቸው ጉዳዮች ዙሪያ መክረዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በማኀበራዊ ትስስር ገጹ እንዳሰፈረው ሁለቱ አካላት ከሁለትዮሽ ግንኙነት ባለፈ በአፍሪካ ቀንድ እና በዓለም አቀፍ ወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያም የጋራ ተጠቃሚነትን በሚያጠናክሩ መስኮች ላይ ተወያይተዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!