የተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) በኢትዮጵያ የቡና ምርት እና ምርታማነት እንዲረጋገጥ እየሠራ መኾኑን ገለጸ።

10

ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የግብርና ሚኒስትሩ ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) በጣሊያን ከሚደገፈው ከተባበሩት መንግሥታት የኢንዱስትሪ ልማት ድርጅት (ዩኒዶ) ፕሮጀክት ፋይናንስ ኦፊሰር ዳፊና ዲሎቫ ጋር ተወያይተዋል። በውይይታቸው ለአየር ንብርት ለውጥ የማይበገር ቡና ልማት ሥራ ላይ በጋራ ለመሥራት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የግብርና ሚኒስትር ግርማ አመንቴ (ዶ.ር) በውይይት ወቅት ኢትዮጵያ ለአየር ንብረት ለውጥ የማይበገር የአርንጓዴ ልማት አቅጣጫን እንደምትከተል ጠቅሰዋል፡፡ ሚኒስትሩ በምሥራቅ አፍሪካ ጥራቱን የጠበቀ ቡና በማምረት ተወዳዳሪነትን መጨመር እና የገበያ መዳረሻዎችን ማሳፋት አስፈላጊ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

ዳፊና ዲሎቫ በበኩላቸው ፕሮጀክቱ ለአየር ንብርት ለውጥ የማይበገር የቡና ልማት ላይ የሚያተኩር መኾኑን ጠቅሰዋል። በቡና እሴት ሰንሰለት፣ በጥራት ማሻሻል፣ የገበያ መዳረሻ በማስፋት እና አርሶ አደሮችን በኩታ ገጠም አደራጅቶ በማሠራት ላይ በትኩረት የሚሠራ መኾኑን ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ፕሮጀክቱ በኢትዮጵያ፣ ኬንያ፣ ታንዛንያ፣ ኡጋንዳ እና ማላዊ እየተተገበረ እንደሚገኝም ኦፊሰሯ አሳውቀዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየሃይማኖት አባቶች ያላቸውን አቅም እና ተደማጭነት በመጠቀም ሰላም እንዲመጣ መሥራት እንዳለባቸው ተጠቆመ።
Next article“በ2016/2017 ከ5 ነጥብ 2 ሚሊዮን ሄክታር በላይ የእርሻ መሬት በዘር ለመሸፈን እየተሠራ ነው” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ