
ባሕር ዳር: ሐምሌ 17/2016 ዓ.ም (አሚኮ)”የምትተክል ሀገር የሚያጸና ትዉልድ፤ ጥላቻን ነቅለን ፍቅር እንተክላለን” በሚል መሪ መልዕክት በሰሜን ወሎ ዞን በሀራ ከተማ 01 ቀበሌ ችግኝ ተከላ ተካሂዷል።
በችግኝ ተከላ መርሐ-ግብሩ የመከላከያ ሠራዊት መሪዎች እና አባላት፣ የሀራ ከተማ መሪዎች፣ የመንግሥት ሠራተኞች እና ነዋሪዎች ተሳትፈዋል። በመርሐ-ግብር ላይ ንግግር ያደረጉት የ802ኛ ኮር አዛዥ ኮሎኔል ቢራራ ሙንዬ ያካሄድነው ችግኝ ተከላ ከምንወደው ሕዝብ ጋር ያለንን ግንኙነት የሚያጠናክር ነው ብለዋል።
የሀራ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ ሙሐመድ ሰዒድ ቂም እና ቁርሾን በመንቀል አንድነትን፣ ሰላምን እና መፈቃቀርን የምናጸናበት ነው ብለዋል። የተከልናቸውን ችግኞች በመንከባከብ ልናጸድቅ ይገባልም ብለዋል። ከንቲባው አያይዘውም የአየር ንብረት ለውጥ የሁሉም አጀንዳ ነው። ለአረንጓዴ አሻራ መርሐ-ግብሩ የድርሻችንን እንወጣ በማለት መልዕክት አስተላልፈዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!