የጎንደር ከተማን ችግር መፍታት የሚቻለው መሪዎች እና የመንግሥት ሰራተኞች ተግባብተው መሥራት ሲችሉ እንደኾነ ተጠቆመ።

15

ጎንደር: ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በጎንደር ከተማ አስተዳደር የክፍለ ከተማ መሪዎች እና መንግሥት ሰራተኞች በወቅታዊ የሰላም ጉደይ ላይ ውይይት አድርገዋል።

ተሳታፊዎቹ የተከሰተው የጸጥታ ችግር በርካታ ማኅበራዊ እና ኢኮኖሚያዊ ቀውስ እያስከተለ መኾኑን ጠቅሰው ክልሉ ከገጠመው ችግር ለመውጣት እና ወደ መደበኛ የልማት ሥራዎች ለመግባት መተማመን እና አንድነት ተገቢ ነው ብለዋል።
ተወያዮቹ የመሪዎች ቁርጠኝነትም ወሳኝ ስለመኾኑ አንስተዋል።

የውይይቱ ተሳታፊዎች በተለይ የመሬት ወረራ፣ ዘረፋ እና መሰል ወንጀሎች እየተበራከቱ መኾኑን ጠቅሰው ለመፍትሄው ሊሠራ እንደሚገባ ተናግረዋል። የብልጽግና ፓርቲ ጎንደር ከተማ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ቻላቸው ዳኘው “የጎንደር ከተማን ችግር መፍታት የሚቻለው መሪዎች እና የመንግሥት ሰራተኞች ተግባብተው መሥራት ሲችሉ ነው” ብለዋል።

የሕዝቡን ጥያቄ ለመፍታት ከመሪዎች ብቻ ሳይኾን ከመንግሥት ሰራተኛውም ይጠበቃል ያሉት አቶ ቻላቸው የመንግሥት ሰራተኛውን ሕይዎት ለማሻሻል እየተሠራ እንደኾነም አብራርተዋል።

ዘጋቢ፦ ተስፋዬ አይጠገብ

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበኢትዮዽያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥታት በትብብር የሚሰጥ ስልጠና መርሐ ግብር ተዋወቀ።
Next article“አማራጭ የለም እየጠላነውም እንኖራለን፤ ከመሞት መሰንበት ይሻላል በሚል” ተፈናቃይ እናት