
ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ አዲስ ለተሾሙ አምባሳደሮች የሥራ ስምሪት እና የልምድ ማካፈል ገለፃ ሰጥተዋል። የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አዲስ ለተሾሙት አምባሳደሮች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ይታወቃል።
በስልጠናው በዛሬ ውሎ ሚኒስትሩ አምባሳደሮቹ በየሚሰማሩባቸው መስኮች እና ሀገራት የኢትዮጵያን ጥቅም እና ክብር በማስከበር ረገድ ሊያከናውኗቸው በሚገቡ የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ፣ የገፅታ ግንባታ እና የባለብዙ መድረክ የዲፕሎማሲ ሥራዎች ላይ ገለጻ አድርገዋል።
በተጨማሪም አምባሳደሮቹ ሊያዳብሯቸው በሚገቡ የግል አሰና የቡድን ክህሎቶች ዙርያ ገለፃ እና መመሪያ መስጠታቸውንም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!