
ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) “የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ” መርሐ ግብር በኢትዮዽያ እና በተባበሩት አረብ ኤምሬትስ መንግሥታት የተጀመረ የዲጂታል ሥራ ክህሎቶችን የማሳደጊያ የትብብር ፕሮጀክት ነው። ፕሮጀክቱ በማደግ ላይ ባለው ዲጂታል ኢኮኖሚ ከባቢ የመጪው ትውልድ ኢትዮጵያዊያንን ለማብቃት ታልሞ የተጀመረ ነው ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም አዲሱን መርሐ ግብር የዲጂታል እውቀትን ክፍተት ለማጥበብ የሚያስችል የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 አካል በማድረግ በይፋ አስጀምረዋል። እንደ አውሮፓዊያን አቆጣጠር በ2026 መርሐ ግብሩ 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንን በዌብ ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እና አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ መሠረታዊ የዲጂታል ክህሎት የሚያስጨብጥ ይኾናል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!