
አዲስ አበባ: ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ችግሮችን መፍታት እና ዘላቂ ልማት ማስፋፋትን ዋና ዓላማ ያደረገው ጉባኤ ከትናንት ጀምሮ በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው። አራተኛው ዓለም አቀፍ ፋይናንስ ለልማት ጉባኤ ዛሬም እንደቀጠለ ነው። ጉባኤው በዛሬው ውሎውም፦
👇የታክስ ገቢን ማሳደግ እና የመንግሥት ፋይናንሺያል አሥተዳደርን በማሻሻል የልማት ሥራዎችን መደገፍ
👇በመንግሥት እና በግሉ ሴክተር መካከል ያለውን ግንኙነት በማሳደግ ለልማት ፕሮጀክቶች ግብዓት የማሰባሰብ አስፈላጊነት
👇በታዳጊ ሀገሮች ላይ ከመጠን ያለፈ የብድር ጫና የሚያስከትሉትን ተግዳሮቶች መፍታት እና ውጤታማ የብድር አያያዝ ስትራቴጂ አስፈላጊነት
👇የአየር ንብረት ለውጥን መቋቋም እና ዘላቂ የአካባቢ ጥበቃ ልምዶችን የሚደግፍ የፋይናንስ ፍላጎትን ማስረፅ
👇ለልማት ምጣኔ ሃብት ተጠያቂነትን ለማረጋገጥ ስለ ዓለም አቀፋዊ ትብብር እና የአሥተዳደር መዋቅር አስፈላጊነት መወያየት።
👇 የልማት የፋይናንስ እጥረቶች እና ኢ-ፍትሃዊነትን መፍታት እና ሁሉን አቀፍ እድገትን ማሳደግ
👇ለልማት ግቦች የሚደረገውን የፋይናንስ ሂደት ለመከታተል የተሻሻሉ የመረጃ አሰባሰብ እና ክትትል ሥርዓቶችን የመዘርጋትን አስፈላጊነት እና መሠል ነጥቦች በተለያዩ ሀገራት መሪዎች እና ተወካዮች የተነሱ ሃሳቦች ናቸው።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!