
ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ)ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) አምሰት ሚሊዮን ዜጎች የዲጂታል ቴክኖሎጂ ስልጠና ተጠቃሚ የሚኾኑበትን አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪን አስጀምረዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ዛሬ በሳይንስ ሙዚየም ኢንሼቲቪን ሲያስጀምሩ እንደገለጹት የኢትዮጵያ የነገ ተስፋዎች የኾኑ ወጣቶች ስልጠናውን በጥሞና በመከታተል ሥራ ፈጣሪ፣ ኩባንያ ፈጣሪና በዓለም ገበያ ተወዳድረው የሚቀጠሩ መኾን ይጠበቅባቸዋል፡፡
ኢንሼቲቩ 5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያ ዘመኑን በዋጀው የዲጂታል ቴክኖሎጂ ተጠቃሚ የሚያደርግ መኾኑን ገልጸው ይህን ትልቅ ዕድል ወጣቶች በአግባቡ በመጠቀም ለኢትዮጵያ የነገ ተስፋ መኾን ይኖርባቸዋል ብለዋል፡፡
እንደ ኢፕድ ዘገባ አምሰት ሚሊዮን የኢትዮጵያ ኮደሮች ኢንሼቲቪ ከተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ ጋር በመተባባር የሚተገበር ሲሆን 5 ሚሊዮን ዜጎች በዲጂታል ቴክኖሎጂ፣ በአርቲፎሻል ኢለጀንሽስ እና በተያያዥ የዲጂታላዜሽን ክህሎቶች የሚሰለጥኑበት መኾኑ ታውቋል፡፡
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!