ኢትዮጵያ ሴቶች ወደ አመራር ሰጪነት እንዲመጡ ውጤታማ ሥራ እየሠራች መኾኑን የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ሙሐመድ ገለጹ።

49

አዲስ አበባ: ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሴቶችን ለማብቃት እና የጾታ እኩልነትን ለማረጋገጥ በኢትዮጵያ ያሉ ተግዳሮቶች እና ዕድሎችን በተመለከተ ከፍተኛ የሀገሪቱ የሴት መሪዎች በተገኙበት ውይይት እየተካሄደ ነው። የሴቶች እና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ኤርጎጌ ተስፋዬ (ዶ.ር) እንደሀገር ሴቶችን ለማብቃት ዘርፈ ብዙ ውጤታማ ሥራዎች ተሠርተዋል ብለዋል።

በተለይም ኢትዮጵያ በቅርቡ የተሸለመችበት ያለ አቻ ጋብቻ እና የሴት ልጅ ግርዛትን በማስቀረት ውጤታማ ሥራን መሥራቱን ጠቅሰዋል። ይሁን እንጂ በገጠር እና በከተማ የሀገሪቱ ክፍል መቀረፍ ያልቻሉ በርካታ ችግሮች አሉ ብለዋል። ሴቶች በሁሉም መስኮች ውጤታማ እንዲኾኑ ያሉባቸውን ጫናዎች ማቅለል በቀጣይ በትኩረት የምንሠራበት ይኾናልም ብለዋል።

የተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና ሙሐመድ ኢትዮጵያ የሴቶችን ተሳትፎ ለማሳደግ ትልቅ የፖለቲካ ቁርጠኝነት መውሰዷን በመግለጽ ይህም በመላው አህጉሪቱ ሊቀጥል የሚገባው መኾኑን አንስተዋል። ለዚህ ደግሞ መንግሥታት ከሲቪል ማኅበራት እና ከሌሎችም አጋር አካላት ጋር ተቀናጅተው መሥራት እንዳለባቸው ገልጸዋል።

ዘጋቢ፡- ቤተልሄም ሰለሞን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ከተመድ ምክትል ዋና ጸሐፊ ጋር ተወያዩ።
Next articleየአፍሪካ የውኃማ አካላት ሳምንት በአዲስ አበባ እየተካሄደ ነው።