
ባሕር ዳር: ሐምሌ 16/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ከተባበሩት መንግስታት ድርጅት ምክትል ዋና ጸሐፊ አሚና መሀመድ ጋር ተወያይተዋል። ውይይቱ የኢትዮጵያ የልማት እንቅስቃሴና የአፍሪካ ቀንድ ቀጣናዊ ጉዳዮች ዙሪያ ያተኮረ መሆኑ ተመላክቷል።
በተጨማሪም መጪውን የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ጉባኤ አስመልክቶ መምከራቸው ተገልጿል።
አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ምክትል ዋና ጸሐፊዋ በተመድ የልማት ሥርዓት ውስጥ እያበረከቱት ስለሚገኘው የአመራርነት ሚና ምድጋና ማቅረባቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በማኅበራዊ ትስስር ገጹ አስታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!