
ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር ተወያዩ።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት በሚያዚያ ወር ከፖለቲካ ፓርቲዎች ተወካዮች ጋር በመገናኘት በሀገራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት አድርገን ነበር ብለዋል። በወቅቱም በየደረጃው ውይይቶች እንዲቀጥሉ አቅጣጫ ተቀምጦ እንደነበርም ጠቅሰዋል።
ዛሬ የሚያዚያው ውይይታችን ቀጣይ የሆነና ሁሉን አቀፍ ጠቀሜታ ባላቸው ሀገራዊ ጉዳዮች መግባባት መፍጠርን የተመለከተ ውይይት አድርገናል ብለዋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!