
ደብረ ማርቆስ: ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በምሥራቅ ጎጀም ዞን የአንድ ቀን የኩታገጠም የስንዴ ዘር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በባሶ ሊበን ወረዳ ተጀምሯል።
በባሶ ሊበን ወረዳ ወረዳ በተጀመረው የኩታ ገጠም የስንዴ ዘር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በአንድ ጀምበር ከ12 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በስንዴ ዘር እንደሚሸፈን የዞኑ ግብርና መምሪያ ኅላፊ አበበ መኮንን ተናግረዋል።
በባሶ ሊበን ወረዳ በተካሄደው የአንድ ጀምበር የኩታ ገጠም የስንዴ ዘር ማስጀመሪያ መርሐ ግብር የምሥራቅ ጎጃም ዞን ምክትል አስተዳደሪ ዋለ አባተን ጨምሮ የመከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ መሪዎች እንዲሁም የዞን እና የወረዳ የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፈዋል።
በ2016/17 የምርት ዘመን በዞኑ በሰብል ከሚሸፈነው ከ600 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት 223 ሺህ ሄክታሩ በስንዴ ዘር እንደሚሸፈን ተነግሯል። ከ10 ሚሊዮን ኩንታል በላይ የስንዴ ምርት እንደሚጠበቅም የዞኑ ግብርና መምሪያ ገልጿል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!