
ባሕር ዳር: ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአማራ ክልል ምክር ቤት የንግድ፣ ኢንዱስትሪ እና ከተማ ልማት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በሥሩ ተጠሪ የኾኑ ተቋማትን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸም እየገመገመ ነው።
የማዕድን ሃብት ልማት፣ ሥራ እና ሥልጠና፣ ከተማ እና መሠረተ ልማት፣ መንገድ፣ ንግድ እና ገበያ ልማት፣ ኢንዱስትሪ እና ኢንቨስትመንት ቢሮዎች እና የትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ ባለሥልጣን ዓመታዊ የሥራ አፈጻጸማቸውን እያቀረቡ ነው።
ቋሚ ኮሚቴው የፈጻሚዎቹን ሪፖርት አድምጦ አቅጣጫ እንደሚሰጥም ይጠበቃል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!