የተተከሉ ችግኞች ፀድቀው ለሀገር ልማት የሚጠቅሙ ለማድረግ ክትትል እንደሚደረግ ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ገለጹ፡፡

18

አዲስ አበባ: ሐምሌ 15/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የዘንድሮውን የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብርን በለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ አካሂዷል። በችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩ ላይ የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ ተገኝተዋል።

በአዲስ አበባ በዓመቱ የችግኝ ተከላ ከ20 ሚሊዮን በላይ ችግኝ ለመትከል ዕቅድ መያዙን የተናግሩት ምክትል ከንቲባ ጃንጥራር ዓባይ በኢንዱስትሪ ቢሮም ከ40 ሺህ በላይ ችግኞችን ለመትከል በመታቀዱ ዛሬ ከ7 ሺህ በላይ ችግኞችን በለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክ እየተተከለ ነው ብለዋል።
የተተከሉ ችግኞች ፀድቀው ለሀገር ልማት የሚጠቅሙ ለማድረግ ክትትል እንደሚደረግላቸውም ተናግረዋል።

የችግኝ ተከላ መርሐ ግብሩን ያካሄዱት የኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ ሠራተኞችም ችግኝን መትከል ብቻ ሳይኾን ሁሉም ለተከለው ችግኝ እንክብካቤ ሊያደርግ ይገባል ብለዋል። በቀጣይም የታቀዱ ችግኞችን በተዘጋጁ ቦታዎች በመትከል ፅዱ እና አረንጓዴ ሀገርን ለትውልድ ለማስረከብ በመርሐ ግብሮች እንደሚሳተፉ ተናገረዋል።

ዘጋቢ፡- ራሔል ደምሰው

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleያለፈው ዓመት የግብዓት አቅርቦት ክፍተት ተፈትቶ ይኾን?
Next articleየሕዝብን የልማት ተጠቃሚነት ለማሳደግ ለአማራ ልማት ማኅበር ድጋፍ ማድረግ እንደሚገባ ተመላከተ፡፡