የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር በ90 ቀን እቅድ ያስገነባቸውን የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አስመረቀ።

116

ባሕር ዳር: ሐምሌ 14/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በአንድ ጎን ልማት እና በሌላ ጎን ሰላምን ለማረጋገጥ ሲሰራ የቆየው የነፋስ መውጫ ከተማ አስተዳደር በ90 ቀን ዕቅድ ያስገነባቸውን የመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች አስመርቋል።

በምረቃ መርሐ ግብሩ የደቡብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ ጥላሁን ደጀኔ፣ የዞኑ ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ መንበር ክፈተው፣ የዞኑ ምክትል አስተዳዳሪ እና የትምህርት መምሪያ ኀላፊን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ተገኝተዋል።

እንደ ዞኑ መንግሥት ኮምዩኒኬሽን መምሪያ መረጃ እንግዶቹ በየመሠረተ ልማቱ ግንባታዎች ላይ አረንጓዴ አሻራቸውን አስቀምጠዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleከ230 ሚሊዮን ብር በላይ ጥቅል ካፒታል ያስመዘገቡ 16 አነስተኛ አምራች ኢንዱስትሪዎች ወደ መካከለኛ ደረጃ ተሸጋገሩ።
Next articleያለፈው ዓመት የግብዓት አቅርቦት ክፍተት ተፈትቶ ይኾን?