“ችግኞችን በመትከልና የደን ሽፋንን በማሳደግ የተጎዱ መሬቶችን ለመጠገን መረባረብ ይገባል” አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ

24

ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ተፈጥሮን ተንከባክቦ የማቆየት ኀላፊነት የሁላችንም ከመኾኑም ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥ ያመጣውን ችግር ለማስተካከል ብቸኛው አማራጭ ነው ሲሉ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ታገሰ ጫፎ ተናገሩ።

“የምትተክል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ ሀሳብ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በተገኙበት የ2016 ዓ.ም የክረምት የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በድሬዳዋ ተካሂዷል።

መርሐ ግብሩ በድሬዳዋ አሥተዳደር ቢዮአዋሌ ክላስተር አዳዳ ገጠር ቀበሌ ተከናውኗል።

አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ በዚህ ወቅቱ ባደረጉት ንግግር፤ ለቀጣዩ ትውልድ ተፈጥሮን ተንከባክበን የማቆየት ኀላፊነት የሁላችንም ከመኾኑም ባሻገር የአየር ንብረት ለውጥ ያመጣውን ችግር ለማስተካከል ብቸኛው አማራጭ ነው ብለዋል።

ዘንድሮ በሚካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር 7 ነጥብ 5 ቢሊየን ችግኞችን በመትከልና የደን ሽፋንን በማሳደግ የተጎዱ መሬቶችን ለመጠገን መረባረብ እንደሚገባ ገልጸዋል።

በመሬት መሸርሸር ምክንያት ምርታማነት በመቀነሱ የአርሶ እና አርብቶ አደሮችን የምግብ ዋስትና በማረጋገጥ በምግብ ሰብል ራስን ለመቻል የሚደረገውን ጥረት ፈታኝ አድርጎት እንደቆየ መጠቆማቸውን ከምክር ቤቱ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ሀገርን ማረጋጋት እና ማፅናት ያስቻሉ የመረጃ ስምሪቶች እና የኦፕሬሽን ሥራዎች ማካሄዱ ተገለጸ።
Next articleበአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር እና የአፍር ክልል ሕዝብን አብሮነት ለማስቀጠል መሥራት እንደሚገባ የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ገለጸ።