
ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በጎንደር ከተማ እየተከናወነ የሚገኘው የኮሪደር ልማት በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ድጋፍና ክትትል እየተደረገ መኾኑን የጎንደር ከተማ አሥተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ ገልጸዋል፡፡
የኮሪደር ልማቱ በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ ከንቲባውን ጨምሮ ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች በሥራዉ እየተሳተፉ የሚገኙ ባለሙያዎችን እና ሠራተኞችን እያበረታቱ ነው።
በጎንደር ከተማ ከሰዓት በፊት በተካሄደው የአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር የገንዘብ ሚኒስትር አሕመድ ሽዴ፣ በምክትል ርእሰ መሥተዳድር ማዕረግ የገጠር ልማት ዘርፍ ዘርፍ አስተባባሪ እና የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ ኀላፊ ድረስ ሳህሉ (ዶ.ር) እና ሌሎች ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች ተሳትፈዋል፡፡
አቶ አሕመድ ሽዴ በታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ተገኝተው በአረንጓዴ አሻራ መርሐ ግብር በመሳተፋቸው መደሰታቸውን ገልጸዋል።
ዘጋቢ፡- አዲስ አለማየሁ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!