
ባሕር ዳር: ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሰሜን ወሎ ዞን በራያ ቆቦ ወረዳ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር “የምትተከል ሀገር የሚያፀና ትውልድ” በሚል መሪ መልእክት እየተካሄደ ነው።
የአካባቢው ማኅበረሰብ፣ የአድማ ብተና እና የወረዳው የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት በ03 አዩብ ቀበሌ የማስጀመሪያ ፕሮግራም መደረጉን የራያ ቆቦ ወረዳ ግብርና ጽሕፈት ኀላፊ ዳኘ ደሳለ ተናግረዋል።
የጽሕፈት ቤቱ ኀላፊ ዳኘ ደሳለ እንዳሉት በ2016 ዓ.ም በ1 ሺህ 713 ሄክታር መሬት ከ 1 ሚሊዮን 327 በላይ ችግኝ መዘጋጀቱን ተናግረዋል።
የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላ መርሐ ግብር በንቅናቄ በወረዳው በሚገኙ 45 ቀበሌዎች የሚቀጥል መኾኑን ከራያ ቆቦ ወረዳ ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!