ሁለቱ ወገኖች ችግሩን ለመፍታት ውይይት እንዲያደርጉ መንገድ ለማመቻቸት የሚያስችል ምክክር እያደረጉ መኾናቸውን የሰላም ካውንስሉ አባላት አስታወቁ፡፡

27

ወልድያ: ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሰሜን ወሎ ዞን እና የወልድያ ከተማ አሥተዳደር የሰላም ካውንስል አባላት ምክክር እያደረጉ ነው።

የሰሜን ወሎ ዞን እና የወልድያ ከተማ አሥተዳደር የሰላም ካውንስል ሠብሣቢ ወርቁ ይመር የተሠባሠብነው ጫካ ያሉ ወንድሞቻችንን ከመንግሥት ጋር ያላቸውን ችግር ለይቶ ምክክር አድርገው እንዲፈቱት ለማመቻቸት ነው ብለዋል፡፡

ሁለቱ ወገኖች ችግሩን ለመፍታት ውይይት እንዲያደርጉ መንገድ ለማመቻቸት የሚያስችል ምክክር እንደሚያደርጉም ገልጸዋል።

የዞኑን ብሎም የክልሉን ችግር እንደ ሕዝብ በመኖር የምናውቀው ነው ብለዋል ሠብሣቢው፡፡ ሕዝቡ ሰላም የሚኾንበት መንገድ ንግግር በመኾኑ ይህ እንዲሳካ የሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ ለመምከር ስለመቀመጣቸውም ነው ያስረዱት።

ሁሉም ወገኖች ሰላም እንዲፈጥሩ ሁሉም የሰላም ካውንስሉ አባላት ገለልተኛ ኾነው እንደሚሰሩ አሳስበዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleየምሥራቅ ጎጃም ዞን እና የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የሰላም ካውንስል አባላት የጋራ የምክክር መድረክ እየተካሄደ ነው።
Next article“በተመረቅንበት የሙያ መስክ ሥራ ፈጣሪ እንጅ ሥራ ጠባቂ አንኾንም” ተመራቂ ተማሪዎች