
ሰቆጣ: ሐምሌ 13/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የሰቆጣ ፖሊ ቲክኒክ ኮሌጅ በቀን እና በማታ መርሐ ግብር ያሠለጠናቸውን 65 ሠልጣኝ ተማሪዎችን አስመርቋል።
ኮሌጁ በ1999 ዓ.ም የተመሠረተ ሲኾን በ2013 ዓ.ም ወደ ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅነት አድጓል።
ከተመሠረተ ለ15ኛ ጊዜ እያስመረቀ የሚገኘው ኮሌጁ በእንሰሳት ተዋጽኦ ዝግጅት፣ በኮምፒውተር ሳይንስ፣ በስትራክቸራል ኮንስትራክሽን እና በመሬት አሥተዳደር ለተከታታይ ሦስት ዓመታት ያሠለጠናቸውን ተማሪዎች ነው ያስመረቀው።
ከተመራቂዎቹ ውስጥ 44ቱ ሠልጣኞች ሴቶች ናቸው።
በምረቃ መርሐ ግብሩ ላይ የዋግኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ሥራ እና ሥልጠና መምሪያ ኀላፊ፣ የሰቆጣ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ፣ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች፣ የኮሌጁ መሪዎች፣ መምህራን እና የተመራቂ ቤተሰቦች ተገኝተዋል።
ዘጋቢ፦ ደጀን ታምሩ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!