የወልድያ ከተማ አሥተዳደር የ2016 የአረንጓዴ አሻራ የችግኝ ተከላን አስጀመረ።

42

ወልድያ: ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) የከተማ አሥተዳደሩ የአረንጓዴ አሻራ ችግኝ ተከላ ማስጀመሪያ መርሐ ግብር በራስ አሊ ክፍለ ከተማ ዋሴ ተፋሰስ ተከናውኗል።

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ግብርና መምሪያ ኀላፊ ደስታ ሞላ ለዚህ ዓመት ከ600 ሺህ በላይ ችግኝ ተዘጋጅቷል ብለዋል። በሁሉም ተፋሰሶች የሚተከሉ ችግኞች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እንዲኖራቸው ታሳቢ ተደርጓል ነው ያሉት።

ከአሁን በፊት የነበሩ የተፋሰስ ልማቶች ሥራ አጥ ወጣቶችን በንብ ሃብት ልማት የሥራ ዕድል እንዲፈጠርላቸው በመደረጉ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ እየተገኘባቸው መኾኑን ገልጸዋል።

የወልድያ ከተማ አሥተዳደር ምክትል ከንቲባ እና የሥራ እና ሥልጠና መምሪያ ኀላፊ አለምነህ ጌጡ ችግኝ እና ተፋሰስን ለመጠበቅ የኅብረተሰቡን ግንዛቤ ማሳደግ እና የጥበቃ ሠራተኛ መቅጠር ላይ ትኩረት ተሰጥቶ እንደሚሠራ ገልጸዋል።

ችግኝ በመትክል ተሳታፊ የነበሩ ነዋሪዎች ችግኝ መትከላቸው ሥነ-ምህዳርን ከመጠበቅ ባሻገር ከተፋሰሶች የሚመጣን ጎርፍ ለመከላከል ያስችላል ነው ያሉት፡፡

ነባር ደንን መጠበቅ እና አዲስ ችግኝ መትከል የመንግሥት እና የኅብረተሰቡ ድርሻ መኾኑንም አስረድተዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“በበጀት ዓመቱ ከ4 ሺህ በላይ ለሚኾኑ ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጓል” የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ
Next articleበ102 ሐሰተኛ የመንጃ ፈቃድ ተጠቃሚዎች ላይ የእርምት እርምጃ ተወስዷል፡፡