
ባሕር ዳር: ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮምቦልቻ ወደ ባሕር ዳር እና ከባሕር ዳር ወደ ኮምቦልቻ በረራ ሊጀመር መኾኑን የኢትዮጵያ አየር መንገድ የኮምቦልቻ ቅርንጫፍ አስታውቋል፡፡
ከኮምቦልቻ ኮሙዩኬሽን ባገኘነው መረጃ መሰረት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከኮምቦልቻ ወደ ባሕር ዳር እና ከባሕር ዳር ወደ ኮምቦልቻ በረራ በመጪው ቅዳሜ ሐምሌ13/2016 ዓ.ም ዳግም እንደሚጀምር ለማወቅ ተችሏል።
በአዲስ መልክ የሚጀመረው በረራ በየቀኑ የሚካሄድ መኾኑም ታውቋል።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!