
ደብረ ብርሃን: ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ እና ጎል ኢትዮጵያ በጋራ በመኾን ያዘጋጁት የኮሌራ ምላሽ እና ንጽህና አጠባበቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።
የደብረ ብርሃን ከተማ አሥተዳደር ጤና መምሪያ ኀላፊ በቀለ ገብሬ ባለፈው ዓመት በከተማ አሥተዳደሩ ተከስቶ የነበረው የኮሌራ በሽታ በዘንድሮው የክረምት ወቅት እንዳይከሰት በንቅናቄ መሥራት ይጠበቃል ብለዋል።
ከተማዋ የቱሪዝም እና የኢንቨስትመንት ፍሰት የሚስተናገድባት በመኾኑ ለበሽታው አጋላጭ የኾኑ ችግሮችን መከላከል እና መቆጣጠር እንደሚያስፈልግም አስገንዝበዋል።
በተፈናቃይ የመጠለያ ጣቢያዎች ላይ የኮሌራ በሽታ መተላለፊያ መንገዶችን በመድፈን ረገድ ተከታታይነት ያላቸው ሥራዎች እንደሚሠሩም ጠቁመዋል።
በውይይት መድረኩ ላይ የተለያዩ ባለድርሻ አካላት እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ዘጋቢ፡- ገንዘብ ታደሰ
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!