
ባሕር ዳር: ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) ከአየርላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጋር ተወያይተዋል።
“ዛሬ የአየርላንድ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር፣ የውጭ ጉዳይ እና መከላከያ ሚኒስትር የኾኑትን ሚካኤል ማርቲን እና ልዑካን ቡድናቸውን አግኝቼ በርከት ባሉ ርእሰ ጉዳዮች ላይ የሁለትዮሽ ውይይት በማድረጌ ደስ ብሎኛል” ነው ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ.ር) በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ላይ ባስተላለፉት መልእክት።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!