የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ለውጥ እያመጣ መኾኑን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ገለጹ፡፡

59

አዲስ አበባ: ሐምሌ 11/2016 ዓ.ም (አሚኮ)በድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር የሚገኙ በከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ተጠቃሚ የኾኑ ነዋሪዎችን የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ ሥራቸውን ጎብኝተዋል።

በፕሮጀክቱ የተሠሩ የልማት ሥራዎች እንደ ጤና ጣቢያ፣ የአንድ ማዕከል አገልግሎት እና የዘላቂ ኑሮ ማሻሻያ ተጠቃሚዎች የጉብኝቱ አካል ናቸው፡፡

በጉብኝቱ ወቅት በልማታዊ የሴፍቲኔት ፕሮግራሙ ተጠቃሚ የኾኑ ነዋሪዎች በፕሮጀክቱ በተሰጣቸው የአቅም ግንባታ፣ የሕይዎት ክህሎት ሥልጠና እና የፋይናንስ ድጋፍ አሁን ላይ ራሳቸውን ከመቻል ባለፈ ቤተሰባቸውን ማሥተዳደር እንዲችሉ እና በዘላቂነት የራሳቸውን ሥራ እንዲጀምሩ እንዳደረጋቸው ተናግረዋል።

የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ የከተማ ልማታዊ ሴፍቲኔት ለውጥ እያመጣ መኾኑን ገልጸዋል፡፡

ጎብኝዎችም በከተሞች መሰል የተሞክሮ ልውውጥ መደረጉ የተሻለ መነሳሳትን ለመፍጠር እንደሚያስችል ተናግረዋል።

በፕሮጀክቱ በአነስተኛ በጀት ለማኅበረሰቡ ትልቅ ለውጥ ማምጣት የሚችሉ የመሠረተ ልማት ሥራዎችን መሥራት እንደሚቻልም ልምድ የወሰዱበት እንደኾነ አስገንዝበዋል፡፡

በጉብኝቱ ላይ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የሚመለከታቸው ከፍተኛ የሥራ ኀላፊዎች፣ የድሬዳዋ ከተማ አሥተዳደር ከፍተኛ መሪዎች፣ የተጠሪ ተቋማት ከፍተኛ ኀላፊዎች፣ የክልል ከተማ እና መሠረተ ልማት ቢሮ ኀላፊዎች፣ የፌዴራል፣ የክልል እና የከተማ አሥተዳደሮች የምግብ ዋስትና የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል።

ተግባራዊ በኾነው የከተሞች ልማታዊ ሴፍቲኔት ፕሮግራም የተለያዩ የልማት ሥራዎች ከመሠራታቸውም ባለፈ በርካታ የከተማዋ ነዋሪዎች በፕሮግራሙ ተጠቃሚ መኾን ችለዋል።

ዘጋቢ፡- ቤቴል መኮንን

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ከ5 ነጥብ 7 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮች ተሰራጭቷል” የአማራ ክልል ግብርና ቢሮ
Next article“አረንጓዴ አሻራ ለነገው ትውልድ የተስፋ እስትንፋስ ነው” የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አሥተዳዳሪ ቢክስ ወርቄ