
ባሕር ዳር: ሐምሌ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም በሚል መሪ ሃሳብ በሁሉም ክፍለ ከተሞች የተካሄደው የሰላም ኮንፈረንስ የማጠቃለያ መድረክ እየተካሄደ ነው፡፡
የከተማ አሥተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ሰለሞን ጌታቸው ባስተላለፉት መልዕክት በክልሉ ያጋጠመውን የጸጥታ ችግር ተከትሎ በርካታ ሰብዓዊ፣ ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ቀውስ ደርሷል።
የጸጥታ ችግሩን በውይይት ለመፍታት የክልሉ መንግሥት አቋም መያዙን ያነሱት አቶ ሰለሞን ይህ ዕውን እንዲኾን ሕዝቡ የጎላ ሚና እንዳለው አንስተዋል።
አቶ ሰለሞን የሕዝቡን ጥያቄ ለማስመለስ በሚል የትጥቅ ትግል የመረጡ ኀይሎች የቀረቡ የሰላም አማራጮችን እንዲቀበሉም ጥሪ አቅርበዋል። የአማራ ሕዝብ ጥያቄ በሰላማዊ ትግል ምላሽ ማግኘት አለበትም ነው ያሉት።
የደብረብርሃን ከተማን ሰላም አስተማማኝ በማድረግ የተነቃቃው የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴ ይበልጥ እንዲያድግ ማድረግ የሚያስችሉ ገንቢ ሃሳቦች ሊንሸራሸሩበት እንደሚችሉም አንስተዋል።
በውይይቱ የኮማንዶ እና አየር ወለድ ምክትል አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል አበባው ሰይድ፣ የ105ኛ ኮማንዶ ክፍለጦር አዛዥ ብርጋዴር ጄኔራል ሞሲሳ ቶሎሳን ጨምሮ የከተማ አሥተዳደሩ የሥራ ኀላፊዎች እና ከሁሉም ክፍለ ከተማ የተውጣጡ የሕዝብ ተወካዮች እየተሳተፉ ይገኛሉ።
ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!