የሀገራዊ ምክክር ሂደት የሚደናቀፍባቸው ዋና ዋና ምክንያቶች ምንድናቸው?

40

ባሕር ዳር፡ ሐምሌ 08/2016 ዓ.ም (አሚኮ) በሀገራዊ ምክክር ዙሪያ በተለያዩ ተቋማት የተደረጉ ጥናቶች ሀገራዊ ምክክር በተለያዩ ምክንያቶች ሊደናቀፍ እንደሚችል ያሳያሉ፡፡ በምክክር ሂደት ውስጥ ያለፉ ሀገራት ተሞክሮዎች ላይ ቅኝት በማድረግ የተሠሩት እነዚህ ጥናቶች ሀገራዊ ምክክር ውጤታማ እንዳይሆንና እንዲደናቀፍ ሊያደርጉ የሚችሉ ከዚህ የሚከተሉትን ሁኔታዎች ይዘረዝራሉ፡፡

👉በተለያዩ ቡድኖች መካከል እጅግ ሰፊ የሆነ የኀይል አለመመጣጠን ሲኖር እና የገነገኑ ኀይሎች (ቡድኖች) አቅማቸውን ተጠቅመው የሀገራዊ ምክክሩን አቅጣጫ የማስቀየር አዝማሚያ ሲያሳዩ፤

👉በምክክር ሂደት ውስጥ ጉልህ ሚና ሊኖራቸው የሚችሉ ባለድርሻ አካላት በአግባቡ ተደራጅተው ሀሳባቸውን ማቅረብ ሳይችሉ ሲቀሩ፤

👉አንዳንድ ባለድርሻ አካላት እና ቡድኖች በሀገራዊ ምክክሩ ሂደት ውስጥ ለመሳተፍ ዝቅተኛ ተነሳሽነት ሲያሳዩ ወይም ጨርሶውኑ ለመሳተፍ ፍቃደኛ ሳይሆኑ ሲቀሩ፤

👉የምክክሩ ሂደት እንዲጠናቀቅ ከፍተኛ የሆነ የግዜ ጫና ሲያጋጥም የሚሉት ናቸው፡፡

ኢትዮጵያ እየመከረች ነው!

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ሀገራ ዊምክክር

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ጎርጎራ ከተፈጥሮ ጋር የተስማማ፣ ታሪክን ግምት ውስጥ ያስገባ፣ ራሱ ታሪክ የኾነ ፕሮጀክት ነው” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next article“ከ7 ሚሊዮን በላይ ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ለመውሰድ ተመዝግበዋል” የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮጀክት ጽሕፈት ቤት