ብልጽግና ፓርቲ የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው።

85

ባሕር ዳር: ሐምሌ 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ብልጽግና ፓርቲ በዋና ጽሕፈት ቤት እና በቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶች በ2016 በጀት ዓመት የተከናወኑ የፓርቲ ሥራዎች የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ይገኛል። ውይይቱ የዓመቱ አፈጻጸም ጥንካሬዎችን በመለየት ለቀጣይ አቅም አድርጎ ለመጠቀም፤ በክፍተት የታዩ ጉዳዮችን በመለየት የማስተካከያ እርምጃዎች መውሰድ እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ማስቀመጥ የሚቻልበት መድረክ መኾኑን የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አደም ፋራህ ተናግረዋል።

ፓርቲው ከላይ እስከ ታችኛው መዋቅር ድረስ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ለመፍጠር የተከናወኑ ተግባራት፣ የእቅዶችን አፈጻጸም ለመገመገም የተካሄዱ የሱፐርሲዥን ሥራዎች እንዲሁም የፓርቲ የተለያዩ የአሠራር ሥርዓቶችን ወጥ ለማድረግ የተዘጋጁ መመሪያዎች ላይ ውይይት እንደሚደረግ ይጠበቃል።

በመድረኩ የብልጽግና ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና የዋና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አደም ፋራህን ጨምሮ የዋና ጽሕፈት ቤት እና የቅርጫፍ ጽሕፈት ቤት መሪዎች እየተሳተፉ መኾኑን ከፓርቲው ማህበራዊ ትስስር ገፅ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“ግጭቱ የዜጎቻችንን ሕይወት አሳጥቶናል፤ በርካታ ቁሳዊ ውድመት ከማስከተል ውጪ ያተረፈልን አንዳችም ነገር የለም” ከንቲባ መንበሩ ዘውዴ
Next articleየመጀመሪያው የኢትዮጵያ ሕገ-መንግሥት