“ግጭቱ የዜጎቻችንን ሕይወት አሳጥቶናል፤ በርካታ ቁሳዊ ውድመት ከማስከተል ውጪ ያተረፈልን አንዳችም ነገር የለም” ከንቲባ መንበሩ ዘውዴ

45

ደብረ ማርቆስ: ሐምሌ 07/2016 ዓ.ም (አሚኮ)”ሰላም ለሁሉም ሁሉም ለሰላም” በሚል ሀሳብ የተዘጋጀው የሰላም ኮንፈረንስ የማጠቃለያ መድረክ በደብረ ማርቆስ ከተማ የከተማው ነዋሪዎችና የተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኀላፊዎች በተገኙበት እየተካሄደ ነው።

በክልሉ የተፈጠረው የፀጥታ ችግር ዘረፈ ብዙ ማኅበራዊ እና ኢኮናሚያዊ ችግሮችን ማሳደሩን የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መንበሩ ዘውዴ ገልጸዋል። “ግጭቱ የዜጎቻችንን ሕይወት አሳጥቶናል፤ በርካታ ቁሳዊ ውድመት ከማስከተል ውጪ ያተረፈልን አንዳችም ነገር የለም” ብለዋል። ከሰላም እጦት ችግር ለመውጣት ሁሉም የሰላም ባለቤት እንዲኾንና የሰላም ካውንስሉ እያደረገ ላለው የውይይት እንቅስቃሴ ተባባሪ እንዲኾንም ከንቲባው ጥሪ አቅርበዋል ።

ኅብረተሰቡ በጫካ ያሉ ወንድሞችን በመምከር መመለስና ለውይይት ራሳቸውን እንዲያዘጋጁ በማድረግ ኀላፊነቱን እንዲወጣም መልእክት አስተላልፈዋል።

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous article“የሕዝባችንን ፍላጎት ለማሟላት በየትኛዉም ጊዜ እና አጋጣሚ ችግሮቻችን በውይይትና በድርድር እንድንፈታ በተደጋጋሚ የሰላም ጥሪ አድርገናል” ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ
Next articleብልጽግና ፓርቲ የ2016 በጀት ዓመት የእቅድ አፈጻጸም ግምገማ እያካሄደ ነው።