
ባለፉት ወራቶች በክልላችን ሕዝብ ላይ የደረሰዉን ስቃይ እኛም ሆነ ጫካ ያሉ ወንድሞቻችን ያዉቁታል፡፡ አሁንም በድጋሜ ለማረጋገጥ የምፈልገዉ ለሰላማዊ አማራጮች በሙሉ በራችን ክፍት ስለመሆኑ ነው፡፡
በመሆኑም ለሕዝባችን ሰላም እና አንድነት፤ ለክልላችን ልማት እና እድገት ስንል በየትኛዉም ቦታ እና ሁኔታ፣ በማንኛዉም አማራጭ ለመወያየት እና ለመደራደር ዝግጁ ነን።
ርእሰ መሥተዳደር አረጋ ከበደ
🕊ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም🕊