የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

32

ባሕር ዳር: ሐምሌ 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ) ነፃ ትራንስፖርት መፈቀዱ አሁን ያለውን የኑሮ ውድነት ጫና ለመቀነስ እንደሚያግዛቸው ሠራተኞቹ ተናግረዋል፡፡

የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ከከተማዋ መስፋት አንፃር የኅብረተሰቡን የትራንስፖርት ፍላጎት ጫና ለመቀነስ ለመንግሥት ሠራተኞች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት እንዲያገኙ ፈቅዷል፡፡

ሠራተኞቹ በሰዓት ገብተው ተገቢውን አገልግሎት ለኅብረተሰቡ እንዲሰጡ እና ሠራተኛውን ከወጭ ለማገዝ በሚል እንደተፈቀደ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ መንበሩ ዘውዴ ገልጸዋል፡፡

ሠራተኞችም በሰዓት በመገኘት ተገልጋዩን ኅብረተሰብ ለማገልገል እንደሚያግዛቸው ተናግረዋል፡፡ ከወጭም እንደሚታደጋቸው አብራርተዋል፡፡

የመንግሥት ሠራተኞች በሳምንት አምስት የሥራ ቀናት ጥዋት እና ምሽት የምሳ ሰዓትን ጨምሮ የተሟላ የትራንስፖርት አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉ ነው የተገለጸው፡፡

ሠራተኞቹ ኅብረተሰቡን በታማኝነት እና በቅንነት ማገልገል አንደሚገባቸውም ተመላክቷል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበክልሉ የተፈጠረው ግጭት በውይይት እንዲፈታ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ፡፡
Next article“መንግሥት እና ታጥቀው ጫካ የገቡ ወገኖች የሰላም ካውንስሉ ያቀረበውን ጥሪ የመቀበል ታሪካዊ ኀላፊነት አለባቸው” የደሴ ከተማ ነዋሪዎች