በክልሉ የተፈጠረው ግጭት በውይይት እንዲፈታ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች ተናገሩ፡፡

61

ደብረ ማርቆስ: ሐምሌ 6/2016 ዓ.ም (አሚኮ)የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች የአካባቢያቸውን ብሎም የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ መክረዋል፡፡

የመንግሥት ሠራተኞቹ “ሰላም ለሁሉም፤ ሁሉም ለሰላም” በሚል መሪ መልዕክት የመነሻ ሃሳብ ቀርቦ በሰላም እና መፍትሄዎች ዙሪያም ውይይት አድርገዋል፡፡

በክልሉ ያጋጠመው የጸጥታ ችግር የሰው ሕይዎት ከማጥፋት ባሻገር የምጣኔ ሃብት እና ማኅበራዊ እንቅስቃሴው ላይ ጉዳትን አስከትሏል፡፡

ችግሩ በዘላቂነት እንዲፈታ እና ሰላም እንዲፈጠር ውይይት ማድረግ ተገቢ መኾኑ ታምኖበት ሥራዎች እየተሠሩ ነው፡፡

ጥያቄ ያላቸው እና የታጠቁ አካላትም ለኅብረተሰቡ ሰላም እና መረጋጋት ሲሉ ወደ ሰላም እንዲመለሱ የበኩላቸውን እንደሚወጡ የደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር የመንግሥት ሠራተኞች በውይይቱ ተናግረዋል፡፡

የከተማ አሥተዳደሩ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ አብተው መኳንንት የመንግሥት ሠራተኞች ከየትኛውም ወገን ያሉትን ልዩነቶች በማጥበብ እና ሰላምን በማረጋገጥ በኩል ኀላፊነታቸውን እንዲወጡ ነው የጠየቁት፡፡

የደብረ ማርቆስ ከማ አሥተዳደር ከንቲባ መንበሩ ዘውዴ መንግሥት በክልሉ ያጋጠመውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት ጥረት እያደረገ መኾኑን ጠቅሰዋል፡፡

እርስ በእርስ ከመጠፋፋት ወጥተን ከገባንበት ምጣኔ ሃብታዊ ድቀት እንድንወጣ የመንግሥት ሠራተኞች የታጠቁ ወንድሞችን ሰላማዊ መንገድን ብቻ ተከትለው ለውይይት እንዲቀርቡ መምከር ይጠበቅባቸዋል ብለዋል፡፡

ለኅብረተሰብ ለውጥ እንተጋለን!

Previous articleበአማራ ክልል የኦሮሞ ብሔረሰብ አሥተዳደር ምክር ቤት የተለያዩ ሹመቶችን ሰጠ።
Next articleየደብረ ማርቆስ ከተማ አሥተዳደር ለመንግሥት ሠራተኞች ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት መስጠት መጀመሩን አስታወቀ፡፡